Kingdom Lifestyle Ministries International
Kingdom Lifestyle Ministries International

ነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች እነማን ናቸው?

ሮሜ 8፡18-19
18የአሁኑ ዘመን ስቃያችን ወደፊት ሊገለጥ ካለው ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ አቆጥራለው፡፡ 19ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል፡፡

እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች እነማን ናቸው ደግሞም ከበስተጀርባቸው በናፍቆት መጠባበቅ ያለው መገለጫቸው ምንድነው? ብዙዎቻችን እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች እኛ አማኞች እንደሆንን እናምናለን፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ ታዋቂ ወንጌላውያን ይመስሉናል፡፡

ከላይ ያየነው ክፍል ሊገለጥ ስላለ ክብር ይናገራል፡፡ ክብሩም እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ብቻ ሊገልጡት የሚችል ይመስላል፡፡ አነጋገሩ ራሱ እንኳን ውስን ለሆነ ቡድን ብቻ እንደሆነ ያመለክታል፡፡

2ቆሮ 3፡9-10 9ሰዎችን የሚኮንነው አገልግሎት የከበረ ከሆነ፤ የሚያጸድቀው አገልግሎት የቱን ያህል ይበልጥ የከበረ ይሆን! 10ከዚህ በፊት ክቡር የነበረው የላቀ ክብር ካለው ጋር ሲወዳደር ክብር የሌለው ሆኖአል፡፡
The word ‘glory’ in these passages and in what the sons of God will manifest is both the same Greek meaning “Doxa”.
በዚህ ክፍል ውስጥ ‹‹ክብር›› የተባለው ቃልና የእግዚአብሔር ልጆች ሊገልጡት ያለው ክብር በአንድ አይነት የግሪክ ቃል ‹‹ዶክሳ›› በሚል የተገለጠ ነው፡፡.

ዶክሳ ትርጉሙ ብርሃናማነትና ማንጸባረቅ፤ መልካም ምስክርነትና ዝና ማለት ነው፡፡

ይህ የእግዚአብሔር ካቦድ ወይም የእርሱ መገኘት ሳይሆን ከቅባት የሚያልፍ ነገር ነው፡፡ በቆሮንቶስ መፅሐፍ ውስጥ በምንመለከትነት ጊዜ ይህ ክብር ልቀት ወይም አሳልፎ መወርወር ወይም መዝለቅ ማለት ነው፡፡

ሊገለጥ ያለው የክብር አይነት ካየነው የሚልቅና የሚልቅ ወይም የላቀ ክብር ነው!

ይህ አይነቱን ክብር ነው እንግዲህ እኛ ከክብር ወደ ክብር የምንለወጥበት፤

ይህ የትንሳኤ ክብር የእኝ የመንፈስን ሰው ከዚህ ደርዝ ወደ ሌላ ደርዝ ያሻግረዋል፡፡ ይኸው ክብር ነው እንግዲህ እግዚአብሔር በእነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ላይ በምድር ላይ ሳሉ በሞታቸው ሳይሆን ለመግለጽ የሚፈልገው፤

ሮሜ 8ን ማንበባችንን ስንቀጥል ይህ አይነቱ ክብር ነጻነትንና ለውጥን የሚያመጣና ሁላችንንም የሚነካና ተጽዕኖ የሚያደርግብን ነው፡፡

ሁላችንም ቤተክርስቲያን እንዲህ አይነቱን ክብር ተሸክማ አለማየታችንን መስማማት እንችላለን፡፡

ቤተክርስቲያን በብርሃናማነትና በማንጸባረቅ፤ በመልካም ምስክርነትና ዝና ገና አላየናትም፡፡

ነገር ግን ይህ መገለጥ የእግዚአብሔር ልጆች እየተሰሩ በሚሔዱበትና መገለጥ በሚጀምሩበት ጊዜ የሚመጣ ይሆናል፡፡

መገለጥ የሚለው ቃል የምንናፍቀው ነገር ነው፡፡ ቃሉ ሜታሞርፎስ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ነው፡፡

ትርጉሙም መውጣት የሚል ሲሆን፡፡ መለወጥ ከሚለው ቃል ተመሳሳይ ቃል ነው፡፡ በውስጥ ተጀምሮ ውጪውን ላይ ተጽዕኖ የሚያደርግን ለውጥ የሚያመለክት ነው፡፡

በዚህ ሜታሞርፎስ የምንጠብቀው ምንድነው፤ ይህን የላቀ ክብር ነው? እንደገና የመክፈቻ ጥቅሳችን እንመልከት፡

ሮሜ 8፡19
19ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል፡፡

በግሪክ መገለጥ ማለት ‹‹መታየት፤ የእውነትና የትዕዛዝ መነገር፤ ክስተቶች በነገሮች ወይም በይዘቶች ወይም ከሰዎች ዕይታ ተሰውረው የነበሩ ለሁሉም መታየት ሲጀምሩ›› ነው፡፡

ይህ መገለጥ እንግዲህ የፈውስ ቅባት ወይም የመነቃቂያ ቅባት አይደለም ነገር ግን ወደ እውነት ወደ መንፈሳችን ዘልቆ በመግባት በውስጣችን ለውጥ የሚፈጥር ነው፡፡

በውስጣችን ሙሉ ስፍራ እንዲይዝ በፈቀድንለት ጊዜ በእኛ በዙሪያ ላሉ ሁሉ የሚታይ የላቀ ክብርን ይለቃል!

2ቆሮ 4፡3-4
3ወንጌላችን ተከደነ ቢሆን እንኳን የተከደነው ለሚጠፉት ነው፡፡ 4የእግዚአብሔር አምሳል የሆነውን የክርስቶስ፤ ወንጌል ብርሃን እንዳያዩ የዚህ አለም አምላክ የማያምኑን ሰዎች ልቦና አሳውሯል፡፡

እውነቱ እውቀት ብቻ አይደለም ነገር ግን ጥልቅ የሆነ በሰዎች አዕምሮ ያለውን የማታለል ጭንብል የሚያነሳም ጭምር ነው፡፡ እናም በወንጌል ያምናሉ! ያ እንግዲህ እውነተኛ ብርሃንና መገለጥ ነው፡፡ ያ ደግሞ ዝናና መልካም ምስክርነት ነው! ያም የተገለጠ እውነት ነው!

የእግዚአብሔር ልጆች ባለፈው ዘመን ተገልጠው ነበር?

መልሱ አዎን ነው፡፡

የቀደመችው ቤተክርስቲያን እንደ ጳውሎስ ያሉ በእንደዚህ አይነቱ መገለጥ በዙሪያቸው ያሉት ልቦች ማርከው የተንቀሳቀሱ ሰዎች ነበሯት፡፡

እንደ ቻርለስ ብርሃናም ያሉ ልሳንን አስመለክቶ ስለ እግዚአብሔር እውነትን ተገንዝበውና እውነቱ በእርሱ እስኪገለጥ ድረስ የጸለዩ ሰዎችን እንመለከታለን፡፡

መገለጡም መጣ የሚልቀው ክብርም ተገለጠ እናም የምድር ስለ እግዚአብሔር ልጆች መገለጥ ጩኸት በሺህ የሚቆጠሩ ከአዙሳ ጎዳናዎች በመፍሰስ ወደ ተልዕኮ ስፍራዎች ተጓዙ፡፡

ውጤቱም ከሰዎች አዕምሮ ጭንብሉ ተነሳ ሰዎችም በወንጌል አመኑ፡፡

ሌሎችም ዱካቸውን ተከተሏቸው፡፡ እንደምታዩት የሚጠይቀው ጥቂቶች ሐዋርያዊ እውነቶችን በመሸከማቸው የሚልቀው ክብር መገለጥ በመጀመር በዙሪያ ያለው ነገር ሁሉ ሲቀየር ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጆች የሚሰራው ሶስት ቀላል ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡

በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ለእውነት በተለያ ደረጃ በቤተክርስቲያን ተኃድሶና በእግዚአብሔር መንግስት ቀዳሚ ሆነው የተመረጡ መሆናቸው ነው፡፡

ሁለተኛ እነዚህ የተመረጡ ሰዎች በእግዚአብሔር በተወሰነ የጊዜ ወሰንና ስፍራ አገልግሎታቸው በአለም ሁሉ ወደፊት እንዲመጣ መታሰባቸው ነው፡፡

ለተግዳሮት የነቁና ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ፤ ሊጠሉ ያሉበትን የተረዱና የሚጸኑ ደግሞም በደስታም የሚጋፈጡ ናቸው፡፡

በመጀመሪያ እውነቱ ህይወታቸውን እንዲዘልቅ ይፈቅዳሉ፤ ቀጥሎም ከእነርሱ ወደሌሎች ይፈሳል፡፡

18የአሁኑ ዘመን ስቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳይደል እቆጥራለሁ፡፡ 19ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል፡፡

በመግቢያችን ከእነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች በትክክል ምን እንደምንጠብቅ አይተናል፡፡ እንደተመለከትነውም እየፈለግነው ያለነው ከውስጥ ጀምሮ ወደ ውጭ ልቆ የሚወጣን ለውጥ እውነትን የሚሸከሙ ሰዎችን ነው፡፡

ደግሞም እንደተመለከትነው እነርሱ ይህ እውነት እንዲያበራና ወይም እንዲያንጸባርቅ በማድረግ ከአፋቸው በሚወጣው ቃል ከማያምኑ ሰዎች የማታለልን ጭንብል እንዲነሳ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ሊገለጥ ያለው ክብር የሚያንጸባርቀው ክብርና ለቤተክርስቲያን ዝናንና መልካም ምስክርነትን የሚያስመልስ ነው፡፡ የላቀ ክብርን ሊያመጣ የሚችል አውነትን ሊገልጥ የሚችል ነው፡፡

ይህን በእኔ የሚሆነው እውነትን ከእግዚአብሔር ክብር ስለ እግዚአብሔር መንግስት በምናገርበት ጊዜ ነው፡፡

ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር መንገዳቸው እንዳቋርጥ እንደላከኝ ይገነዘባሉ፡፡

የእግዚአብሔርን ልጆች ከሌሎች ልዩ የሚያደርጓቸው 3 መለያዎች ምንድን ናቸው?

በእውነት መገለጥ ቀዳሚነት

በተወሰነ የጊዜ ቀመር በእግዚአብሔር የተመረጡና የተቀመጡ ሰዎች መሆናቸው

ለተግዳሮት የነቁና ለሚያስፈልገው መስዋዕትነት የተዘጋጁ

ከዚህ ቀጥሎ የተመለከተው የእነዚህ የእግዚአብሔር ሰዎችን መግለጫና ማንነትን ይሸፍናል

በእግዚአብሔር መንፈስ መመራት!

ሮሜ 8፡14
14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እንዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡

‹‹የሚመሩ›› የሚለው ቃል በተለመደ አማርኛ ቋንቋ ከምናስበው ያለፈ ትርጉም ያለው ነው፡፡ እርግጥ ነው ‹‹መመራት›› አንድ ሰው ወይም ተከታይ ያለውን መከተል ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ‹‹በመያዝ መመራት፤ በዚህ መንገድ ወደ ፍጻሜ መድረስ፤ አብሮ በመሆን ወደ ስፍራ መመራት እንደ ተሳታፊ ራስን ማያያዝ›› ማለትም ጭምር ነው፡፡

ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አጋር በመሆን ሙሉ ለሙሉ እንዲቆጣጠረን መፍቀድ፤

እግዚአብሔር ለአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ፍጻሜያችን በእውነት በሚገለጥበት ሒደት ሁሉ እንደመራን መፍቀድ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን መያዝ ነው እንጂ እኛ አቅጣጫውንና ፍጻሜያችን ሊይዘው የሚገባውን መንገድ የምንወስንበት አይደለም፡፡

‹‹ድንቅን ነው! እግዚአብሔር ቃሉን ወይም ስጦታዎቹን ወይም ምስክርነትን እንድናገር ተጠቀመብኝ! ከሚል አነጋገር ያለፈ ነው›› ከዚህ እጅግ የላቀ ነው! በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን በእግዚአብሔር መንፈስ ህልውና እያንዳንዱ ቅፅበት በሚወስደውን አቅጣጫ ሙሉ ለሙሉ መጠቅለል ነው፡፡

ንጽህናና ክርስቶስ መምሰል

1ዮሐ 3፡1-3
1የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትርፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምነኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ነን፡፡ ዓለም እኛም የማያውቀንም እርሱን ስላላወቀው ነው፡፡ 2ወዳጆች ሆይ እኛ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን ወደፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም እርሱ በሚገለጥበት ጊዜ እናየዋለን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፡፡ 3በእርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹህ እንደሆነ ራሱን ያነጻል፡፡

የእግዚአብሔር አላማ ለእኛ ልጆች ብሎ መጠራት ነው የዚህ ምክንያቱ ደግሞ እርሱ እኛን መውደዱ ነው፡፡

ቅባት አይደለም ወይም የመንፈስ ስጦታዎች ወዘተ ነገር ግን የእግዚአብሔር ምንም ላይ መሰረት ያላደረገ ፍቅር ማናቸውም አይነት ጥረትን የማይጠይቅ ነው፡፡

በቁጥር 2 ላይ ያለው ‹‹እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን›› የሚለው ዓረፍተ ነገር

ይህ ማንነታችን በተመለከተ ያለውን ጥያቄ በመመለስ እና የክርስቶስ ነጸብራቅ ማንነታችንን እንዲሰርጽ በመፍቀድ ለእኛ የሚመጣ ነው፡፡

በመቀጠልም ከዚህ የሚቃረን ዓረፍተ ነገር የሚናገር ይመስላል፡፡

እንዲህ ይላል ‹‹ወደፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም››

‹‹አልተገለጠም›› የሚለው ቃል በሮሜ መጽሐፍ ላይ ስለ እግዚአብሔር ልጆች በመገለጥ ስለ ሚያደርጉት ከተገለጠ ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

‹‹አልተገለጠም›› የሚለው ቃል ‹‹መግለጥ፤ ግልጽ ማድረግ ወይም ተሰውሮ ወይም ሳይታወቅ የነበረውን ማወቅ፤ በግልጽ መታወቅ፤ ሙሉ ለሙሉ መገንዘብ››

ይታያችኋል በመጀመሪያ ልጆች የመሆንን ሒደትንና እውነቱ በውስጣችን ይቀመጥ ዘንድ ልንፈቅድ ይገባል፡፡

ሁላችንም የእግዚአብሔር ልጆች ነን ነገር ግን የተወሰኑ እንዲህ ያለውን ክብርን የሚገልጡ ልጆችን ቡድን እየተጠባበቅን ነው፡፡

እንግዲህ አሁን ምን እንደምሆን ገና አልተገለጠም ተብሎ የተጻፈበት ምክንያት በሒደት ላይ በመሆናችን የተነሳ ነው ፡፡

አንዳንዶች እውነትን ይገልጣሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ላይገልጡ ይችላሉ፡፡ በቁጥር 3 ላይ ወሳኝ የሆነውን ነገር ይሰጣል፡፡ ንጽህና ሒደቱ (ተስፋው) እንዲገልጥ የምንፈቅድበት መንገድ ነው፡፡ ውጤቱ ምናልባትም ዋንኛው ነገርና የእግዚአብሔር ልጆች ሙሉ ለሙሉ መገለጥ ማረጋገጫ ነው፡፡

ከመገለጥ በላይ ያለ ትርጉም ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ሲገለጡ ይታያሉ፤ ይታወቃሉ፤ ግንዛቤን ያገኛሉ፡፡ ያም ዝናንና መልካም ምስክርነትን ከቤተክርስቲያን አይደለም! ነገር ግን ለቤተክርስቲያን! ያመጣሉ፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ስልጣን

1ዮሐ 1፡12-13
12ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው፡፡ 13እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከስጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም፡፡

በእውነት የእግዚአብሔር ልጆች በመሆን ሒደት ውስጥ የመጀመሪያው ደረጃ እርሱን መቀበል ነው፡፡ ይህ ግን የደህንነት ጸሎት አይደለም፡፡ አልያም እርሱ ሊሰጠን ያለውን ነገር ለመቀበል ውሳኔም አይደለም፡፡ እርሱን በውስጣችን መያዝ እና እርሱን መኖር ነው! እርሱን የመውረስ መብት ነው፡፡

‹መቀበል› የሚለው ቃል በእጅ መያዝ፤ አንድን ሰው ወይም ነገርን ለመጠቀም መያዝ፤ ይዞ ለመሔድ መያዝ፤ የራስ ማድረግ፤ ከአንድ ሰው እንደ ጋር አጋር መተባበር፤ መያዝ፤ማድነቅ ማለት ነው፡፡

ጳውሎስ በእግዚአብሔር የተያዝኩበትን የሚለውን ቃል ተመልከቱ፡፡ እግዚአብሔር አይደለም ጳውሎስን የያዘው ነገር ግን ጳውሎስ የሚለው ክርስቶስን አጥብቄ ይዣለው እናም በክርስቶስ ውስጥ ያለውን በሙሉ የመጠቀም ፍላጎት አለኝ ነው!

ይህም ማለት ኃይሉ (የመውረስ መብቱ) የሚመጣው እርሱን እንደተሰጠን በመኖር በመያዝ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ፍጻሜያችንን በመሙላት ወይም በእግዚአብሔር ፈቃድ (መፈጸም ማቋረጥ ሳያስፈልግ) ውስጥ እንድንሆን ያደርገናል፡፡

እንደ ብርሃን ማብራት ከእግዚአብሔር ቃል መገለጥ የተነሳ

ፊሊጲ 2፡14-16
14ማንኛውንም ነገር ሳታጉረመርሙና ሳትከራከሩ አድርጉ፡፡ 15ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹህና ያለ ነቀፋ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው፡፡ 16የህይወትን ቃል ስታቀርቡ በከንቱ እንዳልሮጥሁ ወይም በከንቱ እንዳልደከምሁ በክርስቶስ ቀን የምመካበት ይሆንልኛል

እነዚህን የእግዚአብሔር ልጆች የሚለየው በእንዚህ ቁጥሮች ተመልክቷል፡፡ ተመልከቱ ስጦታ ወይም ካሪዝማ አይደለም ነገር ግን ትክክለኝነትና ባህሪ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች ያለ ነቀፋ፤ ከስህተት ወይም ከእንከን የነጹ ናቸው፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች ጉዳት የማያደርሱ፤ ያልተቀላቀሉ፤ ንጹህ እንደ ወይን ወይም ብረት፤ ከክፉ ጋር ያልተቀላቀሉ፤ ከአታላይነት የጸዱ ወይም ቅኖች ናቸው፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች ተግሳጽ የማስፈልገውን፤ ከነቀፋ የጸዳ ህይወትን ይመራሉ፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች እንደ ብርሃን ያበራሉ፤ በብርሃናማነትና በልቀት ያንጸባርቃሉ፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች የህይወትን ቃል ይይዛሉ ደግሞም ያከብሩታል፡፡

ሮሜ 8፡13-19
13እንደ ስጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞታላችሁና ክፉ የሆነውን የስጋ ስራ በመንፈስ የምትገድሉ ከሆነ ግን በህይወት ትኖራላችሁ፡፡ 14በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡ 15እንደገና የፍርሃት ባሪያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ ሳይሆን አባ አባት ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋልና፡፡ 16የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ሆኖ ይመሰክርልናል፡፡
17ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን የክብሩ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ በእርግጥ የመከራው ተካፋዮች ብንሆን የእግዚአብሔር ወራሾች፤ ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን፡፡ 18የአሁኑ ዘመን ስቃያችን ወደፊት ሊገለጥ ካለው ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እንቆጥራለን፡፡ 19ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች መከራ የሚቀበሉበት ብቸኛ ጊዜ እግዚአብሔር በእነርሱ የሚወልደውን በሚገልጡበት ጊዜ ነው፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር በእኛ ሊወልደው የሚፈልገው ክብር በመከራ ፍጹም ይሆናል፡፡

ይህ ክብር በዙሪያችን ካሉ ነገሮች ሁሉ ጋር ተቃርኖ አለው፤ ከዚህም የተነሳ መገለጡን እንክዳለን፡፡

ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች ስማቸውን ለማጣት ይፈቅዳሉ፡፡

መገለጥን አዲስ መሆነ መንገድ ይይዙና ይገልጣሉ፡፡

ሰዎች የሰሩትን ሃይማኖታዊ መዋቅር ለመጋፈጥ አዲስ መገለጥንና እውነትን በመግለጥ በምድር ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በውስጣቸው ያለው እውነት ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ መለቀቅን ስለሚጠይቅና ሁሉም ነገር ላይ ማፍራትን ከማምጣቱ የተነሳ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ሐሰተኝነትን ይጋፈጣሉ፡፡

Article translated by Benyam Aklog Wondemu

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *